Arts TVArts TV
← NewsEconomy

ጉምሩክ ባላወጣው ጨረታ አታሎ የጨረታ ማስከበሪያ ለመቀበል የሞከረው ግለሰብ ተያዘ

Arts TV · ኤፕሪ 8 2019

ጉምሩክ ባላወጣው ጨረታ አታሎ የጨረታ ማስከበሪያ ለመቀበል የሞከረው ግለሰብ ተያዘ

ጉምሩክ ባላወጣው ጨረታ አታሎ የጨረታ ማስከበሪያ ለመቀበል የሞከረው ግለሰብ ተያዘrnrnነዋሪነቱ አዲስ አበባ የሆነው ይህ ግለሰብ ነጋዴዎችን አነጋግሮ በጉምሩክ ለጨረታ የቀረበ የግንባታ ብረት እንዳለ በማስመሰል አታሎ ገንዘብ ሊቀበል ሲል ጅግጅጋ ላይ ተይዟል።rnrnበጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የስራ ሃላፊዎች ስም የጨረታ ኮሚቴ ነኝ በማለት ለጨረታ ማስከበሪያ በሚል የሀሰት ማሳመኛ 690 ሺህ ብር ሊቀበል ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል።rnግለሰቡ ነጋዴዎችን ለማታለል የሞከረው ለጨረታ የቀረበ 2 ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ ኪ.ግ የግንባታ ብረት በመኖሩ በአነስተኛ ዋጋ አሸናፊ ትሆናላችሁ በማለት ነው።rnጥርጣሬ ያደረባቸው ነጋዴዎችም ወደ ጅግጅጋ ጉምሩክ በማምራት ለማጣራት ባደረጉት ጥረት ግለሰቡ ሊያዝ ችሏል።rnግለሰቡ ከአዲስ አበባ እስከ ጅግጅጋ ኔትወርክ በመዘርጋት ካልተያዙ ሌሎች ግብረአበሮቹ ጋር በመሆን ነው የማታለል እና የማጭበርበር ድርጊት ሲፈፀም የተደረሰበት።rnየጉምሩክ ኮሚሽን ህብረተሰቡ ከአጭበርባሪዎች እንዲጠነቀቅና በተቋማት ስም ክፍያ ሲጠየቅ ከመክፈሉ አስቀድሞ ማረጋገጥ እንዳለበት ጥሪውን አስተላልፏል።

More in Economy