የፊቼ ጫምባላላ በዓል በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ነውrnrnየሲዳማ ብሄር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በዓል በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ነው።rnrnዛሬና የጀመረዉ የሲዳማ ብሄር ዘመን መለወጫ ፊቼ ጫምባላላ በሀዋሳ ከተማ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል።rnrnየፊቼ ጫምባላላ በዓል እየተከበረ የሚገኘውም በዓሉን በሚያንፀባርቁ የተለያዩ ባህላዊ ስነስረዓቶች ነው።rnrnዛሬ በሀዋሳ በሚከናወነው የፊቼ ጫምባላላ በዓል ስነ ስርዓት ላይ የሲዳማ ብሄር ባህልና ቋንቋ የተመለከተ ሲምፖዚዬም ይካሄዳል።rnrnየሲዳማ ሕዝብ የዘመን መለወጫ በዓል ፊቼ ጫምባላላ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) አለም አቀፍ ቅርስ ሆኖ መመዝገቡ የሚታወቅ ነው።rnrnበዓሉ ነገም ተከብሮ ይዉላል፡፡






