የጦር መሳርያ ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙት የ81 ዓመቱ አዛውንት በፅኑ እስራት ተቀጡ።rnአቶ አለማየሁ ቦኩ ሆርዶፋ የተባሉ የ81 ዓመት እድሜ ያላቸዉ ተከሳሽ የወንጀል ህግ አንቀፅ 481 (ሀ) ላይ የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ፍቃድ ሳይኖራቸው ወይም ሕግን ተቃራኒ በሆነ መንገድ መጋቢት 07/2011 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ሲሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ልዩ ቦታው አጣና ተራ እፎይታ አካባቢ በአጠቃላይ 1022 ብር( አንድ ሺህ ሃያ ሁለት ብር) የሚገመቱ የተለያዩ የጦር መሳርያ ጥይቶችን ሽያጭ ሲፈፅሙ የተገኙ በመሆኑ በፈፀሙት የጦር መሳርያ መነገድ ወንጀል በአቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶባቸዋል ።rnrnከሳሽ ዐቃቤ ህግም ለፌደራሉ የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ወንጀል ችሎት የተከሳሽን ጥፋተኝነት ያስረዱልኛል ያላቸውን ዝርዝር የሰው ፣ የሰነድና የኢግዚቪት ማስረጃዎች በማቅረቡና በማስረዳቱ ተከሳሽ ክሱን ማስተባበል ባለመቻላቸው ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት ግንቦት 13/2011 ዓ.ም በዋለው ችሎት በተከሳሽ ላይ የየቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል።rnrnየእስራት እርከኑን በእርከን 10 ስር በመያዝ ተከሳሹ ከዚህ ቀደም የነበራቸው መልካም ባህሪ ፣ የቤተሰብ አስተዳዳሪና በእርጅና ምክንያ የአይን ታማሚ መሆናቸው ሶስት ማቅለያ ተይዞላቸው በእስራት እርከን 7 ፍቃደ ስልጣን ተከሳሹ በ1 ዓመት ፅኑ እስራት አንዲቀጡ ተወስኖባቸዋል ።rnrnምንጭ ፤- የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ






