Arts TVArts TV
← NewsPolitics

የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ /ሳድክ/ ዚምባቡዌ ማእቀብ እንዲነሳላት ጥሪ አቀረበ፡፡

Arts TV · ኦገስ 19 2019

የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ /ሳድክ/ ዚምባቡዌ ማእቀብ እንዲነሳላት ጥሪ አቀረበ፡፡

የደቡባዊ አፍሪካ የልማት ማህበረሰብ /ሳድክ/ ዚምባቡዌ ማእቀብ እንዲነሳላት ጥሪ አቀረበ፡፡rnrnበደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት የተቋቋመው እና 16 ሀገራት በአባልነት የተካተቱበት ሳድክ የአውሮፓ ህብረት እና አሜሪካ በዚምባቡዌ ላይ የጣሉት ማእቀብ በአስቸኳ እንዲነሳ ጠይቋል፡፡rnrnየወቅቱ የሳድክ ሊቀመንበር የሆኑት የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጆን ማጉፉሊ ባስተላለፉት መልእክት ዚምባቡየን በማእቀብ ሳቢያ የገጠማት ችግር ለቀጠናው ሀገራትም የሚተርፍ በመሆኑ  ሊታሰብበት ይገባል ብለዋል፡፡rnrnዚምብቡዌ አሁን በአዲስ የአስተዳደር ዘይቤ ውስጥ እንደሆነች እና ወደፊት ለመራመድ ዝግጁ መሆኗን ከግምት ውስጥ በማስገባት ምእራባዊያን የጣሉባትን ማእቀብ ሊያነሱላት ይገባልም ብለዋል ሊቀመንበሩ፡፡rnrnፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ በበኩላቸው ማእቀቡ የገሪቱን ልማት በእጅጉ እንዳዳከመው በመጥቀስ ይህን ያደረጉ ሀገራትን ወቅሰዋል፡፡rnrnበዚምብቡዌ በአሁኑ ወቅት በተከሰተው የዋጋ ግሽበት ሳቢያ የነዳጅ፣ የሀይል እና የመሰረታዊ ሸቀጦች ዋጋ በማሻቀቡ ህዝቡ መበመንግስት ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ እያነሳ ነው፡፡rnrnአሜሪካ ብቻ 141 የበዚምባቡዌ ተቋማት እና ባለ ስልጣናት ላይ ማእቀብ መጣሏ እና  ባለፈው መጋቢት ይህንኑ ማእቀብ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ፕሬዝዳንት ዶናልድ ተራምፕ መወሰናቸው ይታወሳል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ

More in Politics