የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላትና የእስልምና ኡለማዎች የኢፍጣር የእራት ግብዣ አደረጉ፡፡rnየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ወ/ት ሌንሳ መኮንን ጋር በመሆን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላትና የእስልምና ኡለማዎች የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ የኢፍጣር የእራት ግብዣ አድርገዋል።rnrnኢትዮጵያ በነብዩ መሃመድ ዘንድ ታላቅ ቦታ እንደነበራት ያስታወሱት ሚኒስትሩ በወቅቱ በገዥዎች ጭቆና ይደርስባቸው የነበሩ ተከታዮቻቸውንም በነጻነት ወደምትኖሩባት የአበሻ አገር ኢትዮጵያ ሂዱ ማለታቸውን አንስተዋል።rnrnረመዳን በኢትዮጵያውያን ብሎም በአለም አቀፉ የሙስሊም ማህበረሰብ ዘንድ ታላቅ በዓል መሆኑን የገለጹት አቶ ገዱ በዚህም ግንኙነታችን በማጠናከር በጋራ ለመስራት የምንነሳሳበት እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።rnrnአዲሱ ትውልድ ድህነትን ለማጥፋት፣ ዴሞክራሲን ለማስፈንና የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ለማድረግ አበክሮ እየሰራ እንደሆነም ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።rnrnየቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ወ/ት ሌንሳ መኮንን በበኩላቸው ኢትዮጵያ በመቻቻል እሴቶቿ ለአለም ምሳሌ መሆኗን ገልጸው ይህ ዝግጅትም ለዚህ እሴት እውቅና የመስጠት አንዱ አካል ነው ብለዋል።rnrnኢትዮጵያ በርካታ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ትውፊታዊ፣ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ቅርሶችና የቱሪስት መስህቦች ያላት አገር መሆኗን በማንሳት የዝግጅቱ ተሳታፊዎችም ይችን የታሪክ ሃብታም አገር እንዲጎበኙ ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉያይ ቃል አቀባይ ጽፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።rnrn
← NewsPolitics
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላትና የእስልምና ኡለማዎች የኢፍጣር የእራት ግብዣ አደረጉ፡፡
Arts TV · ሜይ 27 2019





