የኦሮሞና የጋምቤላ ሕዝቦች የወንድማማችነትና የአንድነት መድረክ እየተካሄደ ነውrnrnየኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳን ጨመሮ የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ተሳታፊዎች በውይይት መድረኩ ለመሳተፍ ትናንት ማምሻውን ጋምቤላ ከተማ ገብተዋል፡፡rnrnየኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደሬሳ ተረፈ ለፋና እንደተናገሩት መድረኩ የሁለቱን ክልል ሕዝቦች ለዘመናት ያላቸውን ሰላማዊ ጉርብትና እና ወንድማማችነትን የበለጠ ለማጠናከር ያግዛል።rnrnበሁለቱ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎችም ሆነ ከክልላቸው ውጭ በኦሮሚያና ጋምቤላ የሚኖሩ የሁለቱ ክልል ሕዝቦች ያላቸው በሰላም አብሮ የመኖር እሴት ለሌሎች አካባቢዎችም አርአያ መሆኑን ምክትል ኃላፊው ጠቅሰዋል።rnrnከዚህም በተጨማሪ ሁለቱ ሕዝቦች በእኩልነት ላይ የተመሰረተና የሕዝቦች ፍትሐዊ ተጠቃሚነት የሰፈነባትን ሀገር ለመገንባት የታገሉና እየታገሉ ያሉ ሕዝቦች መሆናቸውንም አንስተዋል።rnrnየውይይት መድረኩ ቀድሞ የነበረውን ወንድማማችነትና አንድነት በማጠናከር የሁለቱን ሕዝቦች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ትስስር በማጎልበት የጋራ የልማት ተጠቃሚነትን በተሻለ ደረጃ ለማረጋገጥ በሚያስችሉ አጀንዳዎች ላይ በመወያየት አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያስችላል ሲሉ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደሬሳ ተረፈ ተናግረዋል።





