Arts TVArts TV
← NewsPolitics

የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት በተቃዋሚዎች ላይ የሀይል እርምጃ መውሰዱ አዲስ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡

Arts TV · ጁን 3 2019

የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት በተቃዋሚዎች ላይ የሀይል እርምጃ መውሰዱ አዲስ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡

የሱዳን ወታደራዊ ምክር ቤት በተቃዋሚዎች ላይ የሀይል እርምጃ መውሰዱ አዲስ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡rnrnየፀጥታ ሀይሎች ለተቃውሞ ጎዳና ላይ የሰነበቱትን ሰዎች ለመበተን ባደረጉት ሙከራ ግጭት ተቀስቅሶ 9 ሰዎች መገደላቸውን አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ በዘገባው አስነብቧል፡፡rnrnህዝባዊ አመፁን በበላይነት የሚመራው የሱዳን ባለ ሞያዎች ማህበር በመላ ሀገሪቱ ለ 48 ሰዓታት የሚቆይ የተቃውሞ ሰልፍ ጠርቷል፡፡rnrnየተቃዋሚዎቹ ቃል አቀባይ ሸሪፍ ሞሀመድ ኦስማን ከባድ መሳሪያ የታጠቁ ሀይሎች በሲቪሎች ላይ ያልተመጣጠነ ሀይል መጠቀማቸውን አውግዘዋል፡፡rnrnበሀገሪቱ ዋነኛ ተቃዋሚ የሚባለው ኡማ ፓርቲ በበኩሉ ወታደራዊ ምክር ቤቱ የጀመረው የሀይል እርምጃ በድርድሩ የቀረችውን የተስፋ ጭላንጭል ያጠፋታል ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡rnrnበምክር ቤቱ እና በተቃዋሚዎች መካከል ተጀምሮ የተቋረጠው ድርድር በፍጥነት እንዲጀመር  ፓርቲው ጥሪ አቅርቧ፡፡rnrnመንገ ሻዓለሙ

More in Politics