የምግብ ዘይት በማምረት የሚታወቀው ጎልደን አፍሪካ የተባለ የማሌዥያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ስራ ሊጀምር ነውrnrn rnrnኩባንያው በኢትዮጵያ የምግብ ዘይት ምርት ላይ ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየቱን ተከትሎ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር ለኩባንያው ሀላፊዎች በዘርፉ ባለው የኢንቬስትመንት እድል ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል ።rnrnበኢትዮጵያ ያለው የምግብ ዘይት ፍላጎት ከፍተኛ ቢሆንም 90 በመቶ የሚደርሰው ምርት ከውጭ አገራት በግዢ የሚገባ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ ፈትለወርቅ በከተማም ሆነ በገጠር የህዝቡ የኑሮ ደረጃ በተሻሻለ ቁጥር የሸማቹ የምግብ ዘይት ፍላጎትና ምርጫ ከፍ ስለሚል በዘርፉ መሰማራት አዋጭ ነው ብለዋል።rnrnከውጭ አገራት የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለሚያመርቱ ኢንቬስተሮች አገሪቱ ጠንካራ የታሪፍ ጥበቃ እንደምታደርግ ሚንስትሯ አብራርተዋል፡፡rnrnየኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፎድ ሀይል በበኩላቸው በኢትዮጵያ ምቹ የኢንቬስትመንት እድሎች በመኖራቸው በምግብ ዘይት ዘርፍ መዋዕለ ንዋያችንን በስራ ላይ ለማዋል ፍላጎት አለን ብለዋል።rnrnኩባንያው በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ የምርት ስራውን እንደሚጀምርና ለ1 ሺህ 500 ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥር በውይይቱ ላይ ተገልጿል።rnrnመረጃውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አግኝተነዋል።rnrn rnrn rnrn rnrn
← NewsEconomy
Economy
Economy
Economy
የምግብ ዘይት በማምረት የሚታወቀው ጎልደን አፍሪካ የተባለ የማሌዥያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ስራ ሊጀምር ነው
Arts TV · ኤፕሪ 23 2019
More in Economy
Economyኢትዮጵያ ባለፉት አስር ወራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና መንግስታት የ4.7 ቢሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ እንዳገኘች የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ጁን 6 2019
Economyበኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ሜይ 10 2019
ARTS
Economyከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
ሜይ 7 2019
Economyየንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ፡፡
ሜይ 7 2019