Arts TVArts TV
← NewsPolitics

የመተከል ዞን ፀጥታ የሚረጋገጠው በሀገር ሽማግሌዎች መሆኑን የአገው ብሔራዌ ሸንጎ አስታወቀ፡፡

Arts TV · ሜይ 7 2019

የመተከል ዞን ፀጥታ የሚረጋገጠው በሀገር ሽማግሌዎች መሆኑን የአገው ብሔራዌ ሸንጎ አስታወቀ፡፡

የመተከል ዞን ፀጥታ የሚረጋገጠው በሀገር ሽማግሌዎች መሆኑን የአገው ብሔራዌ ሸንጎ አስታወቀ፡፡rnrnየመተከል ዞን ፀጥታ የሚረጋገጠው በተፅእኖ ፈጣሪ የሀገር  ሽማግሌዎች  መፍትሄ ሰጪነት  መሆኑን የአገው ብሔራዌ ሸንጎ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ ገልጿል፡፡rnrnበመተከል ዞን  ሰሞኑን የተከሰተው  የሰብአዊ ቀውስና የፀጥታ ችግር  የሚፈታው  ከነዋሪዎች  በሚመነጭ  የሰላም ፍላጎት እና በተፅእኖ ፈጣሪ  የሀገር ሽማግሌዎች መሆኑም  ተነግሯል፡፡rnrnየአገው ብሔራዊ ሸንጎ ለአርትስ ቲቪ በላከው መግለጫ እንደገለፀው የጉምዝ ፤ የሽናሻ ፤ የኦሮሞ እና የአማራ ህዝቦች  የአንድነትን እና አብሮ የመኖር ባህልን  የተላበሰ ማህበረሰብ ነው ያለ ሲሆን ፤ ሰሞኑን በተከሰተው ሰብአዊ ቀውስና የሰው ህይወት ህልፈት  ሸንጎው የተሰማውን  ጥልቅ ሀዘን ገልፃôል፡፡rnrnበመተከል ዞን   ግጭት   እንዲፈጠር ያደረጉ ሃይሎች ድብቅ አለማቸውን በህዝብ  ደም ለማሳካት የሚሞክሩ ፅንፈኛ ሃይሎች  የፈጠሩት  እንደሆነ  በመግለፅ፤ ሸንጎው እነዚህ ሀይሎች ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ  አሳስቧል፡፡rnrnየመከላከያ ወደ አካባቢው መግባትን የገለፀው ብሔራዊ ሸንጎው ፤ የመከላከያ ወደ አካባቢው መግባት ችግሩን ለመፍታት  መልካም ቢሆንም ለችግሩ  ፀጥታ መረጋገጥና  ዋንኛ መፍተሄ ለማምጣት  ከመተከል  ህዝብ  የሚቀድም የለም ብሏል  ፡፡rnrnበመሆኑም ከሁለቱም ክልሎች እና ከተሞች የሀገር ሽማግሌዎችን በመላክ  ችግሩ ወደ ተከሰተባቸው ወረዳዎች እና ቀበሌዎች በመላክ ከፀጥታ አካለት ጋር በመተባበር  ባህላዊ የእርቅ አና  የግጭት አፈታት  ስርዓትን በመከተል ችግሮችን የመፍታት ስራ እንዲሰሩ ሸንጎው ጥሪ አቅርቧል፡፡rnrnይህ በእንዲህ እንዳለ የቢንሻንጉል ጉሙዝ  ብሔራዊ  ክልላዊ መንግስት የዜጎቹን ሰባዊና  ዲሞክራሲያዊ መብቶች  ለማሰጠበቅ  የተማôላ  ህገ መንግስታዊ ስልጣን  ያለው በመሆኑ  ትንኮሳን  አደብ ሊያስገዛ እንደሚገባ ሸንጎው አሳስቧል፡፡rnrnበመጨረሻም በአካባቢው በተከሰተው ግጭት ምክንያት ከቤት ንበረታቸው የተፈናቀሉ ዜጎቸን ወደነበሩበት ለመመለስ  ከሚመከለከታቸው  አካለት ጋር በጋራ እየሰራ እንሚገኝም ነው ሸንጎው በመግለጫው የጠቆመዉ፡፡rnrn 

More in Politics