ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ለመወሰን የሚያስችል ረቂቅ ፍኖተ ካርታ ላይ አውደ ጥናት ተካሂደ፡፡rnrnየሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ አውደ ጥናቱን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ የመሰረተ ልማትና ኢንድስትሪ ፓርኮችን በማስፋፋት በኩል ጥሩ እምርታ ብታስመዘግብም ፤ተቀጥረው የሚሰሩ በርካታ ሰራተኞች በሚከፈላቸው ደመወዝ ቅሬታ እንደሚያሰሙና መንግስት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲወስን የሚጠይቁበት ሁኔታ እንዳለ ተናግረዋል፡፡rnrnዝቅተኛ የደመወዝ ወለል መወሰን ውስብስብ በመሆኑና የአሰሪውም ሆነ የሰራተኛው እይታወች የተለያዮ በመሆናቸው መንግስት የተለያዩ ሀገራት ተሞክሮዎችን በመውሰድ ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ፍትሀዊ ውሳኔ መስጠት እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡rnየውይይት አውደ ጥናቱም በረቂቅ ደረጃ የተዘጋጀውን ፍኖተ ካርታ በማዳበር ሀገራችን ለምትወስነው ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል መጠን አከፋፈል ስርዓት የመሰረት ድንጋይ የሚጥል ጅማሮ እንደሚሆን ሚኒስትሯ ገልጸዋል፡፡rnrnየዓለም ስራ ድርጅት የኢትዮጵያ ተጠሪ ዶክተር አሌክሶ ሙሲንዶ በበኮላቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የኢትዮጵያ መንግስት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል መጠንን ለመወሰን የጀመረው ስራ የሚበረታታና አድናቆት የሚቸረው መሆኑና ለዚህም የዓለም ስራ ድርጅት ድጋፍ እንደሚያደርግ ጠቆመዋል፡፡rnrnየኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ አሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት አቶ ታደለ ይመር በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት የኮንፌዴሬሽኑ አባላት በዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ፅንስ አሳብ ላይ ችግር እንደሌለባቸውና ለሀገራችን ስራ መጎልበት ከሁላችንም የሚጠበቀውን ማድረግ እንደሚገባና ከዚህም በተጨማሪ ከዩንቨርስቲ ተምረው ለሚወጡም ሆነ ለሌሎች ሥራ አጥ ዜጉች ስራ መፍጠርና ወደ ስራ ማስገባት ሌላው አብይ ትኩረት ልንሰጠውና በጋራ ልንሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡rnrnየኢትዮጵያ አሰሪዎች ኮንፌዴሬሽን ፕሬዘዳንት ኢንጅነር ጌታሁን ሁሴን በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል መጠን የመወሰን ጉዳይ ወቅታዊ መሆኑንና ይህም ለኢንዱስትሪውና ለሠራተኛው የስራ መነቃቃት እንደሚፈጥር ጠቁመዋል፡፡rnrnዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ለመወሰን የተዘጋጀው ረቂቅ የአሰራር ፍኖተ ካርታን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ተግባር ለማሸጋገር ሁሉም ባለድርሻ አካላት በጋራ እንዲረባረቡ ጠይቀዋል፡፡rnrn
← NewsSocial
ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ለመወሰን የሚያስችል ረቂቅ ፍኖተ ካርታ ላይ አውደ ጥናት ተካሂደ፡፡
Arts TV · ሜይ 20 2019






