Arts TVArts TV
← NewsEconomy

ከግብር ጋር የተያያዙ 14 አዳዲስና ነባር መመርያዎች ተሻሽለው ፀደቁ

Arts TV · ሜይ 2 2019

ከግብር ጋር የተያያዙ 14 አዳዲስና ነባር መመርያዎች ተሻሽለው ፀደቁ

ከግብር ጋር የተያያዙ 14 አዳዲስና ነባር መመርያዎች ተሻሽለው ፀደቁrnrnየገቢዎች ሚኒስቴር እና የገንዘብ ሚኒስቴር ከግብር ጋር የተያያዙ 14 አዳዲስና ነባር መመርያዎችን አሻሽለው በማፅደቅ ወደ ሥራ እንዲገቡ መወሰናቸው ተነግሯል፡፡rnrnበገቢዎች ሚኒስቴር ከወጡት መመርያዎች ውስጥ፣ ከተከፋይ ሒሳብ የንግድ ትርፍ ግብር ቀንሰው እንዲያስቀሩ ኃላፊነት የተሰጣቸው ታክስ ከፋዮችን ለመወሰን የወጣው መመርያ አንዱ ነው፡፡rnrnየንግድ ሥራ ከተቋረጠ በኋላ በተገኘ ገቢ ላይ ግብር ስለሚከፈልበት ሁኔታ በገቢዎች ሚኒስቴር መመርያ የወጣ ሲሆን፣ የታክስ ክፍያ ጊዜ ማራዘምን የተመለከተው ሚኒስቴሩ ካወጣቸው መመርያዎች ውስጥ የሚጠቀስ ነው፡፡rnrnከተከፋይ ሒሳብ ላይ ሁለት በመቶ የንግድ ትርፍ ግብር ቀንሰው እንዲያስቀሩ ኃላፊነት ከተሰጣቸው ድርጅቶችና መሥሪያ ቤቶች በተጨማሪ፣ ሰፊ የአገር ውስጥ ግብይት ላላቸው ግለሰብ ግብር ከፋዮች ኃላፊነቱን በመስጠት የሚሠራበት ይሆናል ነው የተባለው፡፡rnrnበገንዘብ ሚኒስቴር በኩል ከወጡት ስድስት መመርያዎች ውስጥ የቅድመ ግብር ክፍያ ሥርዓት አፈጻጸም፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመላሽ ስለሚሆንበት መመርያና የታክስ ከፋዩን ሀብት ስለመያዝና ስለመሸጥ የወጡት መመርያዎች ይገኙበታል፡፡rnrnከዚህ በተጨማሪ በታክስ አስተዳደር አዋጁም በድርጅቶችና መሥሪያ ቤቶች ላይ የተጣሉ አስተዳደራዊ ቅጣቶች እና የወንጀል ድንጋጌዎች ተፈጻሚ እንደሚሆኑም ማሻሻያዎቹ ላይ ተቀምጧል፡፡ ሪፖረትር እንደዘገበው፡፡

More in Economy