ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሃቢታት ፕሮግራም ዋና ስራ አስፈፃሚ ቦርድ አባል ሆና ተመረጠችrnrnከየተባበሩት መንግስታት ድርጅት አጠቃላይ የማሻሻያ ሂደት ውጤት የሆነውና በናይሮቢ የተጀመረው የ1ኛው የተባበሩት መንግስታት ድጅት የሃቢታት ጉባኤ ኢትዮጵያን የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ቦርድ አባል አድርጎ መርጧል ሲል የኢትዮጵያ ኢንባሲ በኪንያ ገልጿል።rnrnኢትዮጵያ የስራ አስፈፃሚውን ቦርድ ለአራት አመታት እ.ኤ.አ ከ2019 – 2022 ድረስ ታገለግላለች።rnኢትዮጵያ የአፍሪካን አቋም በመደገፍና በማራመድ በኩል ያላትን የፀና አቋም ለአፍሪካውያን የኩራት ምንጭ እንደሆነ አገራችንን ለቦታው በማጨት መግለፃቸው አገራችን በአፍሪካውያን ዘንድ ያላት የላቀ ተቀባይነት መቀጠሉን ማሳያ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡rnrnኢትዮጵያም ለዚህ ምስጋናዋን በስራ አስፈፃሚ ቦርዱ ላይ የአፍሪካን አቋም በማንፀባረቅ ገልፃለች።rnበኬንያ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ፣ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር ኢንጅነር አይሻ፣ የኢትዮጵያ የልዑካን ቡድን መሪ ስም፣ ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አለን መልዕክቱን አስተላልፏል።
← NewsSocial
ኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሃቢታት ፕሮግራም ዋና ስራ አስፈፃሚ ቦርድ አባል ሆና ተመረጠች
Arts TV · ሜይ 28 2019






