Arts TVArts TV
← NewsEconomy

ኢትሃድ አየር መንገድ በታሪኩ ገጥሞት የማያውቀው ኪሳራ ውስጥ ገብቷል፡፡

Arts TV · ማርች 18 2019

ኢትሃድ አየር መንገድ በታሪኩ ገጥሞት የማያውቀው ኪሳራ ውስጥ ገብቷል፡፡

ኢትሃድ አየር መንገድ በታሪኩ ገጥሞት የማያውቀው ኪሳራ ውስጥ ገብቷል፡፡rnrnንብረትነቱ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የሆነው ኢትሃድ አየር መንገድ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት 1.8 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ እንዳጋጠመው ይፋ አድርጓል፡፡rnrnይህም ጠቅላላ ገቢው በ2017 ከነበረው ጋር ሲነፃፀር በ2.4 በመቶ ዝቅ ማለቱን ያሳያል ነው የተባለው፡፡rnrnሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው አየር መንገዱ በ2017 ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢው 6 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን በ2018 ወደ 5.6 ዶላር ቢሊዮን ገደማ  ወርዷል፡፡rnrnየኪሳራው ምክንያት የመንገደኞች መቀነስ ሲሆን እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2017 18.6 ሚሊዮን መንገደኞችን ያጓጓዘው አየር መንገዱ በቀጣዩ ዓመት ግን የመንገደኞች ቁጥር ወደ 17 .8 ሚሊዮን ዝቅ ማለቱን  ተናግሯል፡፡rnrnከዚህ በተጨማሪም ኢትሃድ አየር መንገድ ከጀርመኑ ኤር በርሊን ጋር በገባው የፍርድ ቤት ክርክር ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ የካሳ ክፍያ  ይጠብቀዋል እየተባለ ነው፡፡rnrn rnrnመንገሻ ዓለሙ

More in Economy