አቶ ደመቀ መኮንን ከፕሬዝዳንት ሙሰቬኒ ጋር ተወያዩrnrnየኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ዛሬ በዩጋንዳ ኢንቴቤ ከተማ ከዩጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ ጋር ተዋያይተዋል።rnrnፕሬዝዳንቱ ኢንቴቤ ከተማ በሚገኘው ፅህፈት ቤታቸው አቶ ደመቀን ተቀብለው አነጋግረዋል።rnrnሁለቱ ከፍተኛ ባለሰልጣናት በቀጠናዊ ትብብር እና በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል።rnrnበተለያዩ መስኮች ለረጅም ዓመታት የዘለቀው የኢትዮጵያ እና የዩጋንዳ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መግባባት ላይ ደርሰዋል።rnrnሁለቱ አገሮች በቀጠናው ዙሪያ በሚስተዋሉ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይም የተወያዩ ሲሆን በቀጣይ በቀጠናው ትብብራቸውን ለማጥጠቅ በሚችሉበት አግባብ ዙሪያ ተስማምተዋል።rnrnአቶ ደመቀ በጉብኝታቸው ከኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለፕሬዚዳንት ሙሴቪኒ ማድረሳቸዉን ከዉጭጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ ቤት ያገኘነዉ መረጃ ያመለክታል




