Arts TVArts TV
← NewsPolitics

አሽራፍ ጋኒ አይ ኤስ አይ ኤስን ለመበቀል ቆርጠን ተነስተናል አሉ፡፡

Arts TV · ኦገስ 19 2019

አሽራፍ ጋኒ አይ ኤስ አይ ኤስን ለመበቀል ቆርጠን ተነስተናል አሉ፡፡

አሽራፍ ጋኒ አይ ኤስ አይ ኤስን ለመበቀል ቆርጠን ተነስተናል አሉ፡፡rnrnፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋኒ ይህን ያሉት አይ ኤስ አይ ኤስ በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ በአንድ የሰርግ ስነ ስርዓት ላይ አደጋ ማድረሱን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ ነው፡፡rnrnአልጀዚራ እንደዘገበው ቡድኑ ለሰርግ በታደሙ ሰዎች ላይ ባደረሰው ጥቃት ከ60 በላይ የሚሆኑት ህይዎታቸው አልፏል፡፡rnrnከሟቾቹ በተጨማሪም 182 ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል ነው የተባለው፡፡ ለደረሰው ጉዳትም አይ ኤስ አይ ኤስ ሃላፊነቱን ወስዷል፡፡rnrnበዚህ ድርጊት ክፉኛ የተበሳጩት ፕሬዝዳንት ጋይን ቡድኑን የገባበት ገብተው ለመቅጣት መዘጋጀታቸውን ገልፀው በዚህ እንቅስቃሴ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከጎናቸው እንዲቆምም ጠይቀዋል፡፡rnrnበአፍጋኒስታን ጥቃቱ የደረሰው አሜሪካ ታሊባኖች እና የሀገሪቱ መንግስት እንዲስማሙ እና ጦሯን ከአፍጋኒስታን ለማስወጣት ውይይት በጀመረችበት ወቅት ነው፡፡rnrnታሊባኖች ከጥቃቱ ጀርባ እንደሌሉበት በመናገር ድርጊቱን ቢያወግዙም ፕሬዝዳንት አሽራፍ ጋኒ ግን ማንም ከደሙ ንፁህ አይደለም ብለዋል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙrnrn 

More in Politics