ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአራት አመት ጊዜ ይጠናቀቃል ፡፡rnrnየግንባታው የመሰረት ድንጋይ ከተጣለ ስምንት ዓመታትን ያስቆጠረው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአራት አመት ጊዜ ይጠናቀቃል ተብሏል ፡፡rnrnየግድቡ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ከተጣለበት ጊዜ አንስቶ መላውን የሀገሪቱን ህዝቦች በጋራ ማንቀሳቀስ የቻለ ፕሮጀክት ነው፡፡rnrnአሁን ላይ የግድቡ የሲቪል ስራ 85 በመቶ ፣የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራ 25 በመቶ እና የብረታብረት ስራ 13 በመቶ ላይ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ፕሮጀክቱ 66 በመቶ ላይ ደርሷል ተብሏል፡፡rnrnከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከግድቡ ግንባታ መዘግየት እና ተያያዥ ችግሮች ምክኒያት የህዝባዊ ተሳትፎ መቀዛቀዝ አሳይቷል ፡፡rnrnበመጀመርያው የግንባታ ጅማሮ ወቅት ትልቅ ሸለቆ በመገኘቱ ግንባታውን በሦስት ዓመታት ማራዘሙ፣ ሜቴክ የኤሌክትሮ ሜካኒካልና የብረታ ብረት ሥራዎች ላይ ባደረገው ማሻሻያ ምክንያት የኮንትራት ማሻሻያ መደረጉ፣ የተጣበበ የኮንትራት ጊዜና የሜቴክ ሥራዎች መዘግየት እንደ ችግር ይነሳሉ፡፡rnrnበመሆኑም ከሜቴክ ጋር የነበረው የሥራ ውል እንዲቋረጥ የተደረገ ሲሆን ፣ ከሜቴክ ጋር በንዑስ ተቋራጭነት ሲሠሩ የነበሩ ተቋራጮችን ሙሉ የኮንትራት ማሻሻያ በማድረግ ወደ ሥራ እንዲገቡና አዳዲስ አምስት ተቋራጮች ቅድመ ክፍያ በመፈጸም ወደ ሥራ እንዲገቡ ተደርጓል፡፡rnrnመንግስት የህዝባዊ ተሳትፎውን እንደገና ለማስጀመር እና ግድቡን በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ መሆኑ ተናግሯል፡፡rnrnታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የመሠረት ድንጋይ የተቀመጠበት 8ኛ ዓመት በጉባ በመከበር ላይ ይገኛል።rnrnየመሠረት ድንጋይ የተቀመጠበት 8ኛ ዓመት የግድቡ ግንባታ እየተካሄደ ባለበት ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጉባ ወረዳ ነው በተለያዩ ስነ ስርዓቶች በመከበር ላይ የሚገኘው።rnrnበክብረ በዓሉ ላይም የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሀይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አብረሃም በላይን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል።rnrn
← NewsEconomy
Economy
Economy
Economy
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በአራት አመት ጊዜ ይጠናቀቃል ፡፡
Arts TV · ኤፕሪ 2 2019

More in Economy
Economyኢትዮጵያ ባለፉት አስር ወራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና መንግስታት የ4.7 ቢሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ እንዳገኘች የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ጁን 6 2019
Economyበኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ሜይ 10 2019
ARTS
Economyከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
ሜይ 7 2019
Economyየንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ፡፡
ሜይ 7 2019

