የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ የመጀመሪያ ግጥሚያ በካምፕ ኑ ላይ በባርሴሎና እና ሊቨርፑል መካከል ተካሂዶ በካታላኑ ቡድን አሸናፊነት ተጠናቅቋል፡፡rnrnየምሽቱን ጨዋታ ባርሳ 3 ለ 0 ሲረታ፤ ሊዮኔል ሜሲ ሁለት ጎሎችን ሲያስቆጥር ቀሪዋን ደግሞ የቀድሞው የቀያዮቹ ተጫዋች ሊዩስ ሱዋሬዝ ከመረብ ጋር አገናኝቷል፡፡rnrnየየርገን ክሎፕ ልጆች በምሽቱ የጨዋታ ብልጫ የነበራቸው እንዲሁም ጥሩ እንቅስቃሴ ቢያደርጉም ከመሸነፍ አልዳኑም፤ ያገኟቸውን መልካም የግብ ዕድሎችን ወደ ጎልነት ቀይረው አለመውጣታቸው የመልሱን ጨዋታ ለመቀልበስ አስቸጋሪ ያደርግባቸዋል፡፡ rnrnየጨዋታው ልዩነት ፈጣሪ እና ኮከብ ተጫዋች ሜሲ በሊቨርፑል መረብ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ጎል ሲያሳርፍ፤ በባርሴሎና መለያ የ14 ዓመት አገልግሎት 600ኛ ጎሉን ማስቆጠር ችሏል፡፡ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ውድድር ደግሞ የእንግዝ ቡድኖች ላይ ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን 26 አድርሷል፡፡rnrnየዘንድሮውን የቻምፒዮንስ ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪንትም አርጀንቲናዊው ኮከብ በ12 ጎሎች እየመራ ይገኛል፡፡rnrnየካታላኑ ባርሴሎና እንደ ክለብ በቻምፒዮንስ ሊጉ ታሪክ 502 ጎሎችን በተቃራኒ መረብ ላይ ማሳረፍ ችሏል፤ ሪያል ማድሪድ 551 ግቦችን በመያዝ ቀዳሚው ክለብ ነው፡፡rnrnቡድኑ ከቀናት በፊት የሊጉን ውድድር ዋንጫ አስቀድሞ ለ26ኛ ጊዜ ማንሳቱ ይታወቃል፡፡rnrnየመልሱ ጨዋታ ቀጣይ ሳምንት ማክሰኞ አንፊልድ ሮድ ላይ ይከናወናል፡፡
← NewsSport
Sport
Sport
Sport
Sport
ባርሴሎና በሜሲ ልዩነት ፈጣሪነት ሊቨርፑልን አሸነፈ
Arts TV · ሜይ 2 2019

More in Sport
Sportበኮፓ አሜሪካ ግማሽ ፍፃሜ ብራዚል ከአርጀንቲና ዛሬ ሌሊት ተጠባቂ ጨዋታ ያደርጋሉ፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportበሴቶች የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ እንግሊዝ ከአሜሪካ የሚያደርጉት የዛሬ ምሽት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
ጁላይ 2 2019
Sportየወጋገን ናትና የ10 ኪ.ሜ የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር ከሰኔ 30 ወደ ሐምሌ 7 እንደተራዘመ ተገለፀ፡፡
ጁላይ 1 2019
Sportበኮፓ አሜሪካ ብራዚል ግማሽ ፍፃሜውን ስትቀላቀል፤ አርጀንቲና ዛሬ ምሽት ተጠባቂ ጨዋታ ይኖራታል፡፡
ጁን 28 2019