Arts TVArts TV
← NewsEconomy

ባለፉት 9 ወራት በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ከተጓጓዙ ከ29 ሚሊየን በላይ መንገደኞች 87 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ተገኝቷል- የትራንስፖርት ሚኒስቴር

Arts TV · ኤፕሪ 23 2019

ባለፉት 9 ወራት በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ከተጓጓዙ ከ29 ሚሊየን በላይ መንገደኞች 87 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር መገኘቱን የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ።rnrn rnrnየክፍያ ጉዳናዎችን በተመለከተም የክፍያ መንገድ ኢንተርፕራይዝ ባለፉት 9 ወራት 6 ሚሊየን 38 ሺህ 800 ተሽከርካሪዎችን ምልልስ በማስተናገድ ከ191 ነጥብ 4 ሚለየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ ተነግሯል።rnrnየትራንስፖርት ሚኒስቴር የ9 ወራት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርቱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት እንደተገለጸው የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ትራንስፖርት ለተጠቃሚዎች ፈጣን አገለግሎት እንዲሰጥ እና ለጉዞም አመቺ እንዲሆን በማሰብ ባቡሮቹ በየጣቢያዎቹ የሚደርሱበትን የጊዜ ረዝማኔ ለመቀነስ ተሞክሯል።rnrnበዚህም መሰረት ከምስራቅ ወደ ምእራብ የሚጓዘውን የባቡር ጉዞ ከ15 ደቂቃ ወደ 12 ደቂቃ ዝግ ማድረግ የተቻለ ሲሆን፥ ከሰሜን ወደደቡብ የሚጓዘውን የባቡር መስመር ደግሞ ከ20 ደቂቃ ወደ 15 ደቂቃ ዝቅ ማድረግ መቻሉ ተገልጿል።rnrnእንደሚኒስቴሩ ሪፖርት ለህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎትን  ተደራሽ ለማድረግ ባለፉት 9 ወራት በተሰራው ስራ የሀገር አቋራጭ አውቶብስ ሰምሪት መስመርን ቁጥር ወደ 223 ከፍ ማድረግ ተችሏል ነው የተባለው።rnrnየመደበኛና ወቅታዊ ከባድ የመንገድ ጥገና ስራዎችን በተመለከተም በ9 ወራት ውስጥ ከ13 ሺህ 228 ኪሎ ሜትር በላይ የመንገድ ጥገና ስራዎች  መከናወናቸው ነው በሚኒስቴሩ ሪፖርት ላይ የተመለከተው ።rnrnበሀገሪቱ የነበረው የፀጥታ ችግር እና የተቋሙ የኮንትራት አስተዳደር አቅም ውስንነት ባለፉት 9 ወራት ላከናወናቸው የመንገድ ጥገና ስራዎች ስኬት እንቅፋት እንደሆኑበት  ሚኒስቴሩ በሪፖርቱ አመልክቷል።

More in Economy