Arts TVArts TV
← NewsEconomy

በጅግጅጋ ቶጎ ውጫሌ የአሜሪካ ዶላርና ጥይቶችን በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

Arts TV · ኤፕሪ 22 2019

በጅግጅጋ ቶጎ ውጫሌ የአሜሪካ ዶላርና ጥይቶችን በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በጅግጅጋ ቶጎ ውጫሌ የአሜሪካ ዶላርና ጥይቶችን በህገወጥ መንገድ ሲያዘዋውሩ የነበሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ ተባለ፡፡rnrnከገቢዎች ሚኒስቴር  እንዳገኘነው መረጃ ለዛሬ አጥቢያ ከሌሊቱ 9 ሰዓት ሲሆን የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-50322 ኦሮ በሆነ ተሽከርካሪ 39 ሺ 700 ዶላር ይዞ ወደ ውጪ ሃገር ሊያስወጣ የነበረ ግለሰብ በቶጎ ውጫሌ የኬላ ተቆጣጣሪዎች ሊያዝ ችሏል ፡፡rnrnግለሰቡ ዶላሩን በጥቁር ፕላስተር ከጠቀለለ በኋላ በሁለቱም እግሮቹ ቡትስ ጫማዎች ውስጥ እንደገበር አድርጎ ሊያሻግር ሲሞክር ነው የተያዘው ተብሏል፡፡rnrnገንዘብ እንደ ጫማ ገበር ተደርጎ ሊወጣ ሲል በዚሁ ኬላ ላይ ለ3ኛ ጊዜ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስነብቧል፡፡rnrnይህ በእንዲህ እንዳ ለዛሬ አጥቢያ ሌሊት በተመሳሳይ ሰዓት በዚሁ ኬላ 41 የማካሮቭ ጥይቶችን በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-54157 ኦሮ መኪና ደብቆ ሊያስወጣ የሞከረ ሌላ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተሰምቷል፡፡

More in Economy