Arts TVArts TV
← NewsSport

በዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ የማራቶን ተወዳዳሪ አትሌቶች ተመርጠዋል፡፡

Arts TV · ሜይ 29 2019

በዶሃ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ የማራቶን ተወዳዳሪ አትሌቶች ተመርጠዋል፡፡
ለ17ኛ ጊዜ በዶሃ ኳታር እ.አ.አ. ከመስከረም 27 እስከ ጥቅምት 6/2019 ዓ. ም. ለሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን የሚወክሉ የማራቶን ቡድን አትሌቶችን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከነተጠባባቂዎቻቸው መርጧል፡፡rnrnአትሌቶቹ በአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (IAAF) ዋና እና የወርቅ ደረጃ በተሰጣቸው ማራቶኖች እ.ኤ.አ ከመስከረም 2018 እስከ ሚያዚያ 2019 ድረስ ተወዳድረው ባስመዘገቡት የተሻለ ሰዓት ተመርጠዋል ብሏል ፌዴሬሽኑ ፡፡rnrnበዚህ መሰረት፡-rnrnበወንዶች፣rn
    rn
  1. አትሌት ሞስነት ገረመው፤ 2019፣ ለንደን፣ 2፡02.55
  2. rn
  3. አትሌት ሙሌ ዋሲሁን፤ 2019፣ ለንደን፣ 2፡03.16
  4. rn
  5. አትሌት ሌሊሳ ዴሲሳ፤ 2018፣ ኒው ዮርክ፣ 2፡05.59
  6. rn
  7. አትሌት ሹራ ኪጣታ፤ 2019፣ ለንደን፣ 2፡05.01 ተጠባባቂ፣
  8. rn
  9. አትሌት ብርሃኑ ለገሰ፤ 2019፣ ቶኪዮ፣ 2፡04.48 ተጠባባቂ፣
  10. rn
  11. አትሌት ታምራት ቶላ፤ 2018፣ ዱባይ፣ 2፡04.06 ተጠባባቂ፣
  12. rn
rnበሴቶች፣ rn
    rn
  1. አትሌት ሩቲ አጋ፤ 2018፣ በርሊን፣ 2፡18.34
  2. rn
  3. አትሌት ወርቅነሽ ደገፋ፤ 2019፣ ዱባይ፣ 2፡17.41
  4. rn
  5. አትሌት ሮዛ ደረጀ፤ 2018፣ ዱባይ፣ 2፡19.17
  6. rn
  7. አትሌት ሹሬ ደምሴ፤ 2019፣ ቶኪዮ፣ 2፡21.05 ተጠባባቂ፣
  8. rn
  9. አትሌት ሄለን ቶላ፤ 2019፣ ቶኪዮ፣ 2፡21.01 ተጠባባቂ ሆነው ተመርጠዋል፡፡
  10. rn
rnከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ባገኘነው መረጃ፤ የሰዓት ልዩነት የሚታየው በአለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር (IAAF) ደረጃ አሰጣጥ መሰረት የማራቶኖቹ ደረጃ ስለሚለያይ መሆኑን እና በምርጫው ቅሬታ ያለው አትሌት ካለ ቅሬታውን በጽሁፍ ለፌዴሬሽኑ እስከሚቀጥለው ሳምንት ግንቦት 27/2011 ዓ. ም ድረስ ማቅረብ ይችላል ተብሏል፡፡

More in Sport