Arts TVArts TV
← NewsSocial

በአሠሪና ሠራተኛ መካከል የተሻለ ግንኙነት እንዲኖር እና ፍትህ እንዲሰፍን መደራጀት  ወሳኝ ነዉ ተባለ፡፡

Arts TV · ሜይ 24 2019

በአሠሪና ሠራተኛ መካከል የተሻለ ግንኙነት እንዲኖር እና ፍትህ እንዲሰፍን መደራጀት  ወሳኝ ነዉ ተባለ፡፡

በአሠሪና ሠራተኛ መካከል የተሻለ ግንኙነት እንዲኖር እና ፍትህ እንዲሰፍን መደራጀት  ወሳኝ ነዉ ተባለ፡፡rnrnየአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነትና አስተዳደር ለማሻሻል በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያም ውይይት ተካሄዷልrnrnየሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን በኢንዱስትሪ ፓርኮች የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነትና አስተዳደር በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡rnrnየምክክር መድረኩ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚገኙ አምራቾች የአሠሪና ሠራተኛ ሕግን በተመለከተ ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግና እየተሻሻለ ባለው የአሠሪና ሠራተኛ ሕግ ላይ አጠቃላይ ምልከታ ለመስጠት ያለመ ነው፡፡rnrnየሠራተኛኛ ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ በመድረኩ መክፈቻ ላይ እንደተናገሩት ለዜጎች ምቹ የስራ እድል በመፍጠር ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ መንግስት እየሰራ መሆኑን ጠቁመው፤ ምቹ የሥራ ሁኔታን በመፍጠር ሂደት የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የሠራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ከባለ ሀብቶች ጋር በጋራ ችግሮችን በመፍታት እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡rnrnሚኒስትሯ የግሉ ዘርፍ ለሀገር እድገት እንደ ኃይል የሚታይ የልማት አጋር በመሆኑ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ጠቁመው፤ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የአሠሪና ሠራተኛ ግንኙነትና አስተዳደር ጋር የተያያዙ ችግሮችን ደረጃ በደረጃ እየፈቱ ለመሄድ የሁለትዮሽ እና የሦሥትዮሽ መድረኮችን በመፍጠር በጋራና በጥምረት ይሰራል ነው ያሉት፡፡rnrnለዚህም እየተከለሰ ባለው የአሠሪና ሠራተኛ ሕግ የሠራተኛው እና የአሠሪው ጥቅምና መብት እንዲከበት የሚያስችል ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ የሠራተኛው መብትና ደህንነት እንዲጠበቅ እና ዝቅጠኛ የደመወዝ ወለል መወሰን የሚያስችሉ ጉዳዮች መካተታቸውን ነው ሚኒስትሯ የተናገሩት፡፡rnrnየኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበበ አበባየሁ በበኩላቸው የአሠሪና ሠራተኛ ሕጉ የሠራተኛውን መብት ባስጠበቀና የሀገሪቱን ለኢንቨስትመንት ተመራጭነት ባልጎዳ መልኩ ማሻሻያ እንደተደረገበት ተናግረዋል፡፡ ሕጉ ዝቅተኛ የደሞዝ መጠን በድርድርና በግልፅ የማስቀመጥ እድል እንደሚሰጥም አክለዋል፡፡rnrnበኢንዱስትሪ ፓርኮች የአሠሪና ሠራተኛ ሕግና አስተዳደር በተመለከተ የመወያያ ጽሑፍ ያቀረቡት በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሠላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክትር የሆኑት አቶ ፍቃዱ ገብሩ በአሠሪና ሠራተኛ መካከል የተሻለ ግንኙነት እንዲኖር እና ማህበራዊ ፍትህ እንዲሰፍን መደራጀት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተናግረዋል፡፡rnrnየአሠሪዎችና ሠራተኞች ተጠቃሚነት በማረጋገጥ የኢንዱስትሩ ሠላምን ለማስፈን እንዲሁም ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ምቹ የሥራ ሁኔታን ለመፍጠር መንግስት የአሠሪና ሠራተኛ ህጉን በማሻሻል ላይ ሲሆን ረቂቅ ሕጉ በሚኒስትሮች ምክርቤት ፀድቆ ለተጨማሪ እይታ ወደ ሚመለከተው የሕግ ክፍል መመራቱ ታውቋል፡፡rnrn 

More in Social