በአማራ ክልል በተለያዩ ወቅቶች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ምክክር መጀመሩ ተነገረ፡፡rnrn በጉባኤው የተገኙት የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለችግሮች የሚመጥን የሕግ ማስከበር ሥራ እንዲኖር ለማስቻል ምክክሩ ለቀጣይ ስምሪቶች ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ገልጸዋል፡፡rnrnምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች እና አጎራባች ስፍራዎች የሕግ የበላይነት እንዲከበር እና ሕዝቡ የሚፈልገውን ሰላም ለማረጋገጥ የፌዴራል እና የክልሉ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች፣ መከላከያ እና ብሔራዊ ደኅንነት ቢሮ በመገኘታቸው ለቀጣይ ስምሪት ከፍተኛ እገዛ እንዳለው ተናግረዋል፡፡rnrnበክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ሲፈጠሩ የቆዩ የፀጥታ ችግሮችን መገምገምን ዓላማ ያደረገው ምክክሩ ለችግሩ የሚመጥን ጠንካራ የሕግ ማስከበር ሥራ ለመሥራት እንደሚያግዝ ታምኖበታል፡፡rnrnከሰሞኑ በቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉር ወረዳ አካባቢ የተከሰተውን ግጭት ለመፍታት የተደራጀ ቡድን ወደ አካባቢው ማምራቱም ተነግሯል፡፡rnrnበዳንጉር አካባቢ የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎም በአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ጃዊ አካባቢ የፀጥታ ችግር መቀስቀሱ ታውቋል፡፡rnrnይህ ውይይት የፀጥታውን ችግር ለመቆጣጠር እና ለዜጎች አስተማማኝ የፀጥታ ዋስትና ለማረጋገጥ የሚደረግ ምክክር መሆኑን የአማራ መገኛኛ ብዙሃን ድርጅት ገልጿል፡፡rnrn rnrn rnrn
← NewsSocial
በአማራ ክልል በተለያዩ ወቅቶች የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል ምክክር መጀመሩ ተነገረ
Arts TV · ኤፕሪ 30 2019