በማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ የሚለቀቁ የሀሰት መረጃዎች በአሁኑ ወቅት ፈተና መሆናቸውን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ተናገሩ፡፡rnrnፕሬዝዳንቷ ይህንን የተናገሩት የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በኢትዮጵያ እየተከበረ ባለበት ወቅት ነዉ፡፡rnrnከረቡዕ ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች መከበር የጀመረው 26ኛውን አለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ቀን፥ በዛሬው እለትም በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በሚካሄድ ውይይት ቀጥሎ ውሏል።rnrnበአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እየተካሄደ ባለው መርሃ ግብር ላይም መገናኛ ብዙሃን በነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲሁም በዴሞክራሲያ ስርዓት ግንባታ ላይ ባላቸው ሚና ላይ ትኩረት በማድረግ ነው እየመከረ ነዉ፡፡rnrnበአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እየተካሄደ ባለው የዓለም ፕሬስ ነፃነት ቀን ላይም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባደረጉት ንግግርም በኢትዮጵያ ከፍተኛ ለውጥ እየተካሄደ መሆኑን በመጥቀስ፤ ለውጡም ለሚዲያው ነፃነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልፀዋል።rnrnኢትዮጵያም በቀጣይ ዓመት ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት ላይ መሆንዋንም ተናግረዋል፡፡rnrnበማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ የሚለቀቁ የሀሰት መረጃዎች በአሁኑ ወቅት ፈተና መሆናቸውን ያነሱት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፤ የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ተሳታፊዎች በማህበራዊ ትስስር ድረ ገፆች የሚለቀቁ የሀሰት መረጃዎችን እንዴት መከላከል ይቻላል የሚለው ላይ ትኩረት አደርገው እንዲመክሩ እና እንዲሰሩም ጠይቀዋል።rnrn
← NewsSocial
በማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ የሚለቀቁ የሀሰት መረጃዎች በአሁኑ ወቅት ፈተና መሆናቸውን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ተናገሩ፡፡
Arts TV · ሜይ 2 2019






