ሱዳን በፀጥታ ችግር ምክንያት ትምህርት ቤቶቿን ዘጋች፡፡rnrnሰሞኑን በኮርዶፋን አካባቢ በተፈጠረው ግጭት ሳቢያ ተማሪዎች መገደላቸው ሱዳናዊያንን አስቆጥቷል፡፡rnrnሮይተርስ እንደዘገበው በመላ ሀገሪቱ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲደረግ ከተቃዋሚዎች ጥሪ ተላልፏል፡፡rnrnውጥረቱ እየተባባሰ መምጣቱ ያሳሰበው የሱዳን ጊዜያዊ ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት የሰዓት እላፊ ገደብ ከመጣል ጀምሮ በሀገሪቱ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላልተወሰነ ጊዜ እንዲዘጉ ወስኗል፡፡rnrnየሽግግር ምክር ቤቱ እና ተቃዋሚዎቹ ለሶስት ዓመት በስራ ላይ የሚቆይ የጋራ የሲቪል አስተዳደር ለመመስረት ወደ ስምምነት በተቃረቡበት ወቅት ይህ ችግር መፈጠሩ የነበረውን ተስፋ አጨልሞታል ተብሏል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ





