ለሀገራችን ኢንዱስትሪ ውጤታማነት በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ተቀናጅቶ መፍታት ይገባል ተባለrnለሀገራችን ኢንዱስሪ ውጤማነት አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎቸ ያሉባቸውን ችግሮች ተቀናጅቶ መፍታት ይገባሉ ሲሉ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚአብሔር ተናገሩrnሚኒስትሯ ይህንን ያሉት ከፌዴራል አነስተኛና መካከለኛ ማኒፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ስትሪንግ ኮሚቴ ጋር በኢንተርኮንቲነንታል ሆቴል በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡rnስትሪንግ ኮሚቴው አነስተኛና መካከለኛ ማኒፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች ውጤታማ እንዳይሆኑ ባደረጓቸው ችግሮች፣በዘርፉ በተሰሩ ስራዎችና ያሉ ችግሮች እንዲሁም በመፍትሄ አምጪ ጉዳዮች ላይ መክሯል፡፡rnrnየሀገሪቷን ኢኮኖሚ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ለማሸጋገር በሚደረገው ጥረት ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን ውጤት እንዳላመጣ የተገመገመ ሲሆን ለዚህም የዳረጉት የአደረጃጀት፣የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽ፣ የፋይናንስ አጠቃቀም እና የሼዶች በአግባቡ ስራ ላይ አለመዋል መሆናቸው በውይይቱ ተጠቅሰዋል፡፡rnrnወ/ሮ ፈትለወርቅ ችግሮቹን ለመፍታት ዘርፉን ለመደገፍ የተቋቋሙ ተቋማት፣ ክልሎች እና ድርሻ ያላቸው ድርጅቶች ተቀናጅው መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡rnrnበፌዴራል ደረጃ የሚደረገው ድጋፍ እንደተጠበቀ ሆኖ የክልሎች ሚና ከፍተኛ ስለሆነ ሊያሰራቸው የሚችለውን አደረጃጀት በመፍጠር ከባለድርሻዎች ጋር ተቀራርቦ መስራት ይኖርባቸዋል ያሉት ሚኒስትሯ በካፒታል እቃዎች ግዥ መጓተት አምራቾችን ከሚደርስባችው አላስፈላጊ ወጪ ለመታደግ እና የውጪ ምንዛሪ ችግርንም ለማቃለል በሀገር ውስጥ የሚመረቱ ማሽኖችንና ግብዓቶችን በመጠቀም ከውጪ የምናስገባቸውን ማሽኖችን መጠን መቀነስ ይገባልም ብለዋል፡፡
← NewsEconomy
Economy
Economy
Economy
ለሀገራችን ኢንዱስትሪ ውጤታማነት በዘርፉ ያሉ ችግሮችን ተቀናጅቶ መፍታት ይገባል ተባለ
Arts TV · ኤፕሪ 1 2019
More in Economy
Economyኢትዮጵያ ባለፉት አስር ወራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና መንግስታት የ4.7 ቢሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ እንዳገኘች የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ጁን 6 2019
Economyበኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ሜይ 10 2019
ARTS
Economyከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
ሜይ 7 2019
Economyየንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ፡፡
ሜይ 7 2019

