ህብረቱ ለኢትዮጵያ ያለውን አድናቆት ገለፀ ፡፡rnrnየአፍሪካ ህብረት ኢትዮጵያ የአፍሪካ አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነት አዋጅን በማፅደቋ ምስጋና ይገባታል አለ፡፡rnrnበህብረቱ የንግድ እና ኢንዱስትሬ ኮሚሽነር አልበርት ሙቻንጋ በቱይተር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ የኢትዮጵያን ውሳኔ ወቅታዊ እና ታሪካዊ በማለት አሞካሽተውታል፡፡rnrnሙቻንጋ ከኢትዮጵያ ፓርላማ ይሄን ውሳኔ መስማት ለህብረቱ ትልቅ እና መልካም ዜና ነው፤ ከእንግዲህ አንድ የአፍሪካ ሀገር ብቻ ስምምነቱን የሀገሩ ህግ አድርጎ ቢያፀድቅ ስራችንን በፍጥነት እንጀምራለን ብለዋል፡፡rnrnየአፍሪካ ህብረት አህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ለመመስረት እንዲችል ቢያንስ 22 ሀገራት ስምምነቱን የራሳቸው ሀገር የህግ አካል አድርገው ማፀደቅ ይጠበቅባቸዋል፡፡rnrnአሁን ኢትዮጵያ 21ኛ ሀገር ሆና ስትፈርም ህብረቱ የወጠነውን ዓለማ ለማሳካት ጫፍ ላይ መድረሱን የሚያመለክት መሆኑ ነው የተነገረው፡፡rnrnአህጉራዊ ነጻ የንግድ ቀጠና ስምምነቱ ተግባራዊ ሲሆን እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2022 በአህጉሪቱ የሚኖረውን የእርስበርስ የንግድ ልውውጥ በ52 በመቶ ከፍ ያደርገዋል ተብሏል፡፡rnrnአፍሪካዊያን በዚህ የንግድ እንቅስቃሴ ሲሳተፉ 90 በመቶ የሚሆነው በሸቀጦች ላይ የሚጣለው ታሪፍ የሚነሳላቸው ሲሆን በአገልግሎት እና በሌሎች ዘርፎች ላይ ያሉ እንቅፋቶችንም ያስወግድላቸዋል፡፡rnrnአፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ይህ ቀጠናዊ ነፃ የንግድ ስምምነት እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣር በ1995 ዓለም አቀፉ የንግድ ድርጅት ከተመሰረተ ወዲህ የተቋቋመ ትልቁ የንግድ ቀጠና ነው፡፡rnrnስምምነቱ በሙሉ አቅሙ ወደ ስራ ሲገባ አመታዊ ሀገራዊ ጥቅል ምርታቸው ከ3 ትሪሊዮን ዶላር በላይ በሚገመት 1.2 ቢሊዮን ደንበኞች መካከል የንግድ ትስስርን ይፈጥራል፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ
← NewsEconomy
Economy
Economy
Economy
ህብረቱ ለኢትዮጵያ ያለውን አድናቆት ገለፀ ፡፡
Arts TV · ማርች 22 2019

More in Economy
Economyኢትዮጵያ ባለፉት አስር ወራት ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት እና መንግስታት የ4.7 ቢሊዮን ዶላር የልማት ድጋፍ እንዳገኘች የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ጁን 6 2019
Economyበኮንትሮባንድ የሚሳተፉ አካላት አስተማሪ እርምጃ ሊወሰድባቸው ይገባል ተባለ፡፡
ሜይ 10 2019
ARTS
Economyከ37.4 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ኮንትሮባንድ ማዕድናት ባለፉት ዘጠኝ መያዙን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ ፡፡
ሜይ 7 2019
Economyየንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ልዩ ትኩረት መስጠቱን ገለጸ፡፡
ሜይ 7 2019

