Arts TVArts TV
← NewsPolitics

ሀምዶክ የመጀመሪያ የውጭ ሀገር ጉብኝታቸውን በጎረቤት ደቡብ ሱዳን ጀምረዋል፡፡

Arts TV · ሴፕቴ 13 2019

ሀምዶክ የመጀመሪያ የውጭ ሀገር ጉብኝታቸውን በጎረቤት ደቡብ ሱዳን ጀምረዋል፡፡

ሀምዶክ የመጀመሪያ የውጭ ሀገር ጉብኝታቸውን በጎረቤት ደቡብ ሱዳን ጀምረዋል፡፡rnrnአዲሱ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሀምዶክ ወደ ጁባ አቅንተው ከፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ጋር በጋራ ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ እየመከሩ ነው፡፡rnrnሮይተርስ እንደዘገበው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሁለት ቀናት የሚቆይ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ነው ወደ ደቡብ ሱዳን የተጓዙት፡፡rnrnበውይይቱ ወቅት ከሱዳኗ አቻቸው አሳም አብደላ ጋር ሆነው መግለጫ የሰጡት የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አውት ዴንግ አኩይል በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ቅራኔ  ለማስቆም ጊዜው አሁን ነው ብለዋል፡፡rnrnሀምዶክ ጁባ እንደደረሱ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ከጎረቤት ደበቡብ ሱዳን ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማጠናከር የትኛውንም ስልት እንከተላለን ብለዋል፡፡rnrnካርቱም እና ጁባ በንግድ፣ በድንበር አካባቢ ያሉ ክርክሮችን በማስወገድ የሁለቱ ሀገራት ህዝቦች በነፃነት እንዲንቀሳቀሱ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተቀራርበው እንዲሰሩ ምክክር መጀመራቸውንም  ተናግረዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡rnrnመንገሻ ዓለሙ

More in Politics