Breaking News

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላትና የእስልምና ኡለማዎች የኢፍጣር የእራት ግብዣ አደረጉ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ወ/ት ሌንሳ መኮንን ጋር በመሆን መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላትና የእስልምና ኡለማዎች የረመዳን ጾምን ምክንያት በማድረግ የኢፍጣር የእራት ግብዣ አድርገዋል።

ኢትዮጵያ በነብዩ መሃመድ ዘንድ ታላቅ ቦታ እንደነበራት ያስታወሱት ሚኒስትሩ  በወቅቱ በገዥዎች ጭቆና ይደርስባቸው የነበሩ ተከታዮቻቸውንም በነጻነት ወደምትኖሩባት የአበሻ አገር ኢትዮጵያ ሂዱ ማለታቸውን አንስተዋል።

ረመዳን በኢትዮጵያውያን ብሎም በአለም አቀፉ የሙስሊም ማህበረሰብ ዘንድ ታላቅ በዓል መሆኑን የገለጹት አቶ ገዱ በዚህም ግንኙነታችን በማጠናከር በጋራ ለመስራት የምንነሳሳበት እንደሚሆን ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

አዲሱ ትውልድ ድህነትን ለማጥፋት፣ ዴሞክራሲን ለማስፈንና የሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ ለማድረግ አበክሮ እየሰራ እንደሆነም ሚኒስትሩ አስታውቀዋል።

የቱሪዝም ኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር ወ/ት ሌንሳ መኮንን በበኩላቸው ኢትዮጵያ በመቻቻል እሴቶቿ ለአለም ምሳሌ መሆኗን ገልጸው ይህ ዝግጅትም ለዚህ እሴት እውቅና የመስጠት አንዱ አካል ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ በርካታ ባህላዊ፣ ሃይማኖታዊ፣ ትውፊታዊ፣ የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ቅርሶችና የቱሪስት መስህቦች ያላት አገር መሆኗን በማንሳት የዝግጅቱ ተሳታፊዎችም ይችን የታሪክ ሃብታም አገር እንዲጎበኙ ጥሪ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉያይ ቃል አቀባይ ጽፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

leave a reply