Breaking News

ሞዛምቢክ ውስጥ የመጀመሪያዎቹ  የኮሌራ ታማሚዎች  ተገኝተዋል፡፡

ከኮሌራ በተጨማሪ የወባ በሽታ እንዳይከሰትም ትልቅ ስጋትን ፈጥሯል፡፡

ሞዛምቢክ ውስጥ የመጀመሪያዎቹ  የኮሌራ ታማሚዎች  ተገኝተዋል፡፡

የሞዛምቢኳ የወደብ ከተማ ቤራ በከባድ አውሎ ነፋስ ከተመታች ወዲህ ነዋሪዎቹ ተፈናቅለው በአንድ ቦታ መከማቸታቸው እና አካባቢው በውሃ በመጥለቅለቁ ሳቢያ ተላላፊ በሽታ እንዳይከሰት ተሰግቶ ነበር፡፡

አሁን የተፈራው አልቀረም የኮሌራ ህመም መከሰቱን የሀገሪቱ ባለ ስልጣናት ይፋ አድርገዋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው በአደጋው ከ 468 በላይ ሰዎች በሞቱባት ሞዛምቢክ  አምስት ሰዎች በኮሌራ ህመም መጠቃታቸው መሀኪሞች ተረጋግጧል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት ችግሩ ይከሰታል የሚል ቅድመ ትንበያ ስለነበረው 900 ሺህ ከኮሌራ ህመም የሚፈውሱ እንክብሎችን ወደ ስፍራው ልኳል፡፡

በደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት የተከሰተው ከባድ ዝናብ ያስከተለው አደጋ በርካታ ቦታዎችን ረግረጋማ እንዲሆኑ በማድረጉ ከኮሌራ በተጨማሪ የወባ በሽታ እንዳይከሰት ትልቅ ስጋትን ፈጥሯል ነው የተባለው፡፡

እስካሁን በሞዛምቢክ፣ በማዊ እና በዚምባቡዌ በአደጋው ምክንያት የሟቾች ቁጥር ከ700 በላይ መድረሱ ተነግሯል፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

leave a reply