Breaking News

ታይላንድ በአዲሱ ዓመት በርካታ ዜጎቿን በትራፍክ አደጋ አጥታለች

ታይላንድ በአዲሱ ዓመት በርካታ ዜጎቿን በትራፍክ አደጋ አጥታለች

 

ታይላንድ በአዲሱ ዓመት በርካታ ዜጎቿን በትራፍክ አደጋ አጥታለች

ታይላንዳዊያን አዲሱን ዓመት ሲቀበሉ ከልክ ያለፈ ፈንጠዝያ ውስጥ በመግባታቸው በሽዎች የሚቆጠሩት የትራፊክ አደጋ ሰለባ ሆነዋል

አለጀዚራ በዘገባው እንዳስነበበው አዲሱ ዓመት ከመግባቱ ከአራት ቀናት ጀምሮ እስከ ሁለተኛው ቀን ድረስ ባለው ጊዜ 463 ሰዎች በትራፊክ አደጋ ህይዎታቸው አልፏል፡፡

ከሟቾቹ መካል 89 የሚሆኑት በበዓሉ እለት የሞቱ ሲሆን አብዛኛውን አደጋ ያደረሱት ደግሞ የሞተር ሳይክ አሽከርካሪዎች ናቸው ተብሏል፡፡

80 በመቶ የሚሆነው የአደጋው መንስኤ ጠጥቶ ከመጠን በላይ ከማሽከርከር ጋር በቀጥታ እንደሚገናኝ የሀገሪቱ ባለ ስልጣናት ተናግረዋል::

በአደጋው ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ አራት ሺህ ሰዎች ከባድ እና ቀላል የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸውም የህገሪቱ አደጋ መከላከል ኤጀንሲ ባወጣው ሪፖርት አመላክቷል፡፡

ታይላንድ ባለፈው ዓመትም አዲስ ዓመት ስታከብር በተመሳሳይ የመንገድ ላይ አደጋ 423 ዜጎቿን አጥታለች፡፡

እንደ አውሮፓወዊያኑ አቆጣጠር በ2015 የወጣ ሪፖርት እንደሚያሳየው ታይላንድ  በትራፊክ አደጋ ብዙ ሰዎች ከሚሞቱባቸው ሀገራት በሁለተኛ ደረጃ ትገኛለች፡፡

 

 

 

leave a reply